=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ከሁሉም ጭንቀታምና ደስታ አልባዎች ማለት የኢማንን ጣዕም ያልቀመሱና የየቂንን (በአሏህ እርግጠኛ የመሆንን) ምንነት የማያውቁ ናቸው። እነዚህ ሁሌም ጭንቀት ፣ ንዴት ፣ ውርደትና ጥበት ውስጥ ናቸው።
-<({አል-ቁርአን 20:124})>-
«ከግሳፄም የዞረ ሰው ለርሱ ጠባብ ኑሮ አለው።»
የአለማቱ ጌታ በሆነው አሏህ ከማመን ውጭ ነፍስን የሚያስደስታት ፣ የሚያጠራት የሚያነፃት ፣ ጭንቀቷንና ጥበቷንም የሚያስወግድላት ነገር የለም። ካለም ኢማን ህይወትና ጣዕም ሊኖራት አይችልም።
የእምነት (ኢማን) አልባዎች ከችግር መላቀቂያና እራሳቸውን ከጭንቀት ፣ የነፋስ ፅልመትና ጉዳት ማረፊያ አይነተኛ ዘዴያቸው ካላመኑ እራሳቸውን ማጥፋት ነው። ኢማን የሌለባት ህይወት ጥፉ እና ክፉ ነች። የአሏህን የህይወት ጎዳና የሚቃረኑት የሚከተላቸው ዘላለማዊ እርግማን ምንኛ የከፋ ነው።
--<({አል-ቁርአን 6:110})>--
«በመጀመሪያም ጊዜ በርሱ እንዳላመኑ ሁሉ ልቦቻቸውን እና ዓይኖቻቸውን እናገላብጣለን ፤ በጥመታቸውም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ እንተዋቸዋለን።»
አዕምሮ ከረጅም እልህ አስጨራሽና ለብዙ ዘመናት ከቆየ ጥናት በኋላ የደረሰበትን የጣኦት ከንቱነት ፣ የክህደትን እርጉምነት እና ውሸተኝነት እንዲሁም የመልእክተኞችን እውነተኝነት እና የአሏህን ሃቅነት ፣ ንግስናና ምስጋና የሱ እንደሆኑና በሁሉም ነገር ላይ ቻይ መሆኑን አይቶ ዓለም በሙሉ በአሏህ ብቸኛ አምላክነት የሚያምንበት ጊዜው አሁን ነው። ደስታህ ፣ ዕረፍትህና እርጋታህ በኢማንህ ጥንካሬና ድክመት ፤ ትኩሰነት እና ቅዝቃዜ ልክ ይሆናል።
--<({አል-ቁርአን 16:97})>--
«ለወንድ ወይም ሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሠራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን ፤ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።»
ይህችም መልካም ኑሮ መገለጫዋ ለጌታቸው መልካም ቃል ኪዳን የነፍሶቻቸው መረጋጋት ፣ ፈጣሪያቸውን በመውደድ የልቦቻቸው መፅናት ፣ ከጥመት ጎዳና የውስጣቸው መጥራት ፣ በችግር ጊዜ ያላቸው ጥንካሬ ፣ የአሏህ ውሳኔ ሲፈጸም የልቦቻቸው አለመጨነቅና በውሳኔውም ደስተኛ ሆኖ መቀበል ናቸው። ምክኒያቱም እነሱ የአሏህን ጌትነት ፣ የኢስላምን ሃይማኖትነት እና የሙሐመድን ሰ.ዐ.ወ ነብይነት ወደው ተቀብለዋልና።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|